✍ አዘጋጅ: አህመድሐጂ ሷዲቅ
አሏህ ሆይ! ስራዬን ተቀበለኝ አባቴንም ማርልኝ!
የቃል አይነትና ሁኔታ (الكلمة والاعراب)… ክፍል-1
* ናህው/نحو የሚባለው የቋንቋ ፊልድ የሚያጠናው የአንድን ቃል የመጨረሻ ሁኔታ ሲሆን "ሶርፍ" ደግሞ የቃሉን መጀመሪያና መሀል ሁኔታ ያጠናል። በናህው መሰረት
* ማንኛውም የአረበኛ ቃል (كلمة) ከ3 አይነት ነገር አንዱ ነው ከዚህ ውጭ አይሆንም።
① ስም/اسم ② ግስ/فعل) ③ ፊደል/حرف
* ማንኛውም የአረበኛ ስም ወይም ግስ ደግሞ የቃሉ የመጨረሻ ሁኔታ (اعراب) ከ4 ነገር አንዱ ነው ከዚህ ውጭ አይሆንም።
① ረፍእ/رفع ② ነስብ/نصب ③ ኸፍድ/خفض ④ ጀዝም/جزم
[ማብራሪያ]
① ረፍእ/رفع የምንለው የቃሉ የመጨረቫ ፊደል በግልፅ የዶማ ምልክት ወይም በድብቅ ዶማን የሚተካ ፊደል (و ا ن ) ሲቀመጥበት ነው።
ለምሳሌ الحمدُ ስንል የቃሉ የመጨረሻው ፊደል ምልክቱ ዶማ ነው ስለዚህ ُالحمد የሚለው ቃል ረፍእ (መርፉእ) ነው ይባላል።
② ነስብ/نصب የምንለው የቃሉ የመጨረቫ ፊደል በግልፅ የፈተሀ ምልክት ወይም ፈተሀን የሚተካ ፊደል (ي ا ن ) ሲቀመጥበት ነው።
ለምሳሌ إنَّ اللهَ ስንል የቃሉ የመጨረሻ ፊደል ምልክቱ ፈተሀ ነው ስለዚህ اللهَ የሚለው ቃል ነስብ (መንሱብ) ነው ይባላል።
③ ኸፍድ/خفض የምንለው የቃሉ የመጨረቫ ፊደል በግልፅ የከስራ ምልክት ወይም በድብቅ ከስራን የሚተካ ፊደል (ي ا) ሲቀመጥበት ነው።
ለምሳሌ بِاللهِ ስንል የቃሉ የመጨረሻ ፊደል ምልክቱ ከስራ ነው ስለዚህ اللهِ የሚለው ቃል ኸፍድ/ከሰራ (መኽፉድ) ነው ይባላል።
④ ጀዝም/جزم የምንለው የቃሉ የመጨረቫ ፊደል በግልፅ የሱኩን ምልክት ሲቀመጥበት ወይም በድብቅ ስኩንን የሚተካ የፊደል መውደቅ ሲከሰትበት ነው።
ለምሳሌ لم يلدْ ስንል የቃሉ የመጨረሻ ፊደል ምልክቱ ስኩን ነው ስለዚህ يلدْ የሚለው ቃል ጀዝም (መጅዙም) ነው ይባላል። #hajnahw

-----------------------
✔የፊደል ምልክቶች (علامات الحروف)
* በናህው እሳቤ ፊደል/حرف የሚለው ቃል ማንኛውንም በአልፋቤት ያለን ፊደል ሳይሆን ከስም እና ከፊዕል ጋር በመገናኘት ትርጉም የሚሰጥን ፊደል ለማለት ነው። (جاء لمعنى)
* ፊደል/حرف እንደ ስምና ፊዕል በራሱ ምልክት የለውም ነገር ግን ማንኛውም ለስምና ለግስ ምልክት ያለሆነ ሁሉ ፊደል/ሀርፍ ሊሆን ይችላል። የፊደል/حرف አይነቶች ብዙ ናቸው ትቂቶቹን ብናይ»
① የነስብ ፊደል/حرف نصب ምሳሌ(أن ، لن)
② የክልከላ ፊደል/حرف نفي ምሳሌ(لا ، لم)
③ የኸፍድ ፊደል/حرف خفض ምሳሌ(من ، الى)
④ የመሀላ ፊደል/حرف قسم ምሳሌ(و ب ت)
⑤ የጀዝም (የስኩን) ፊደል/حرف جزم ምሳሌ(لم ، ألم)
⑥ የመጠየቂያ ፊደል/حرف إستفهام ምሳሌ(هل ، أ)
⑦ የማስከተያ ፊደል/ حرف عطف ምሳሌ(و ، ثم)
⑧ የማስቀሪያ ፊደል/حرف استثناء ምሳሌ(إلا ، سوى)
⑨ የመልስ ፊደል/حرف جواب ምሳሌ(بلى ، ف)
---------------------------------
✔የረፍዕ ምልክቶች…(علامات الرفع) ክፍል 1
* 4ቱም የኢዕራብ አይነቶች (رفع ، نصب ، خفض ، جزم) ምልክታቸው በ 2 ይከፈላል።
① ግልፅ ወይም ዋና ምልክት/ظاهر እና
② የዋናው ምልክት ምትክ/نيابة
[የዶማ ምትክ፣ የፈተሀ መትክ፣ የከስራ ምትክና የጀዝም ምትክ]
* የረፍእ ምልክተች (علامات الرفع) 4 ናቸው። [ضوان ብለን በአጭሩ መያዝ እንችላለን]
* ዋናው የረፍእ/رفع ምልክት ዶማ/ضمة ነው ዶማ ደግም 4 ቦታ ላይ በግልፅ (በይፋ) ለረፍእ ምልክት ትሆናለች።
ሀ) ነጠላ ስም/اسم المفزد ላይ
* ምሳሌ جاء رجلٌ ብንል رجلٌ የሚለው በግልፅ ዶማ/ضمة ظاهرة ረፍእ ሆኗል።
ለ) ወጥ-ያልሆነ የወንዶች ብዙ ቁጥር/جمع التكسير ላይ
ምሳሌ ُجاء الرجال ስንል رجال ወጥ-ያልሆነ የወንዶች ብዙ ቁጥር ስለሆነ በግልፅ ዶማ ረፍእ ሆኗል።
ሐ) ወጥ-የሆነ የሴቶች ብዙ ቁጥር/جمع مؤنث سالم
ምሳሌ جاء المؤمناتُ ብንል ُمؤمنات ወጥ-የሆነ የሴቶች ብዙ ቁጥር ስለሆነ በግልፅ ዶማ ረፍእ ሆኗል።
መ) መጨረሻው ያልተያዘ (صحيح) የወደፊት ጊዜ ግስ (فعل مضارع) [Future Tense]
* ምሳሌ الله يعلمُ ብንል يعلمُ መጨረሻው ያልተያዘ (صحيح) ሶሂህ ግስ ስለሆነ በግልፅ ዶማ ረፍእ ሆኗል።
---------------------
✔አሁን ደግሞ ዋና ምልክቱን ዶማን በመተካት ለረፍእ ምልክት የሚሆኑ ሀርፎችንና ምልክት የሚሆኑበትን ቦታ እናያለን። [ዋን/وان ብለን 3ቱን ሀርፎች በእጭሩ መያዝ ይቻላል] ① ዋው/واو ② አሊፍ/ألف እና ③ የኑን መገኘት (ثبوت النون) ናቸው።
① ሐርፍ ዋው/واو በሁለት ቦታ ላይ ለረፍእ ምልክት ይሆናል።
ሀ) ወጥ-የሆነ የወንዶች ብዙ ቁጥር (جمع مذكر سالم)
ምሳሌ جاء المؤمنون ብንል المؤمنون ወጥ-የሆነ የወንዶች ብዙ ቁጥር ስለሆነ ዶማን በመተካት በዋው ሀርፍ ረፍእ ሆኗል [وعلامة رفعه الواو نيابة عن الضمة]
ለ) አምስቱ ስሞች (أسماء الخمسة)
* አምስቱ ስሞች የሚባሉት: አባትህ፣ እህትህ… [أَبُوكَ، وَأَخُوكَ، وَحَمُوكَ، وَفُوكَ، وَذُو مَالٍ]
ምሳሌ جاء أخوك ብንል أخوك ከአምስቱ ስሞች አንዱ ስለሆነ ዶማን በመተካት በዋው (و) ሀርፍ ረፍእ ሆኗል።
----------------------
② አሊፍ/ألف በአንድ ቦታ ላይ ብቻ ዶማን በመተካ ለረፍእ ምልክት ይሆናል እሱም ጥንድ ስም/مثنى (dual) ወይም تثنية الاسماء ይባላል።
ምሳሌ جاء الرجلان ብንል رحلان ጥንድ ስም/مثنى ስለሆነ ዶማን በመተካት በአሊፍ (ا) ሀርፍ የረፍእ ምልክት ሆኗል [وعلامة رفعه الالف نيابة عن الضنة]
---------------------
③ የኑን ፊደል መገኘት (ثبوت النون) በአንድ ቦታ ላይ ብቻ ዶማን በመተካ ለረፍእ ምልክት ይሆናል እሱም አምስቱ ስሞች/ أفعل الخمسة ነው። አምስቱ ስሞች/أفعل الخمسة የሚባሉት (يضربون ، تضربون ، يضربان ، تضربان ، تضربين) ናቸው። ምሳሌ َأَنتُم تَضْربُون ብንል تَضْربُون ከአምስቱ ሰሪ ግሶች/أفعال الخمسة አንዱ ስለሆነ በቃሉ መጨረሻ ላይ በመጣችው የኑን ፊደል (ن) ለረፍእ ምልክት ሆናለች [وعلامة رفعه ثبوت النون نيابة عن الضمة] #hajnahw


=======
✔የነስብ ምልክቶች…(علامات النصب) ክፍል 2
* ነስብ/نصب አምስት ምልክቶች አሉት፤ ዋና (አስልይ) ምልክቱ ፈተሀ/فتحة ሲሆን ሌሎች ፈተሀን ተክተው/نيابة عن الفتحة የሚመጡ 4 ምልክቶችም አሉት። በአጭሩ فكيان ብለን መያዝ እንችላለን።
① ፈተሀ/فتحة በግልፅ/ظاهر ለነስብ ምልክት የሚሆንባቸው 3 ቦታውዎች አሉ።
☞ሀ) ነጠላ ስም/اسم المفرد)
ምሳሌ رَأيتُ رجلاً ብንል رَجلاً ነጠላ ስም (اسم مفرد) ስለሆነ በግልፅ የፈተሀ ምልክት ነስብ ሆኗል።
[وعلامة نصبه فتحة ظاهرة ]
☞ለ) ወጥ-ያልሆነ የወንዶች ብዙ ቁጠር/جمع التكسير
ምሳሌ َرأيتُ الرجال የሚለውን ብናይ الرجالَ ወጥ-ያልሆነ የወንዶች ብዙ ቁጠር/جمع التكسير ስለሆነ በግልፅ ፈተሀ ለነስብ ምልክት ሆኗል።
[ወጥ-ያልሆነ የወንዶች ብዙ ቁጠር ማለት ስሙ ወደ ፕሉላር ፎርም ሲቀየር አንድ አይነት ፓተርን የለለው።
☞ሐ) የወደፊት ጊዜ/future ግስ/ فعل المضارع ላይ የነስብ ፊደል ሲገባ።
ምሳሌ لَنْ يَضْرِبَ የሚለውን ብናል يضربَ የወደፊት ጊዜ ግስ/فعل المضارع ስለሆነ በግልፅ ፈተሀ ለነስብ ምልክት ሆኗል።
………………………
② ከስራ/كسرة በፈተሀ ምትክ/نيابة عن الفتحة ለነስብ ምልክት የሚሆነው አንድ ቦታ ላይ ነው እሱም»
☞ሀ) ወጥ-የሆነ የሴቶች ብዙ ቁጥር/جمع مؤنث سالم ላይ ነው።
ምሳሌ رَئيتُ المُؤمِناتِ ብንል المؤمناتِ ወጥ-የሆነ የሴቶች ብዙ ቁጥር/جمع مؤنث سالم ስለሆነ በፈተሀ ምትክ ከስራ ለነስብ ምልክት ሆኗል። [وعلامت نصبه كسرة نيابة عن الفتحة]
{ከላይ ያሉት 2ቱ የሀረካ/حركة ምልክቶቹ ሲሆኑ 3ቱ የሀርፍ/حرف ምልክቶች ደገሞ እኒህ ናቸው።}
③ የያእ ፊደል/الياء (ፈተሀን በመተካት) ለነስብ ምልክት ሆኖ የሚመጣው 2 ቦታ ላይ ነው።
☞ ሀ) ወጥ-የሆነ የወንዶች ብዙ ቁጥር/جمع مذكر سالم
ምሳሌ رأيتُ المُسلِمِينَ ብንል المُسلِمِينَ ወጥ-የሆነ የወንዶች ብዙ ቁጥር/جمع مذكر سالم ስለሆነ በፈተሀ ምትክ በሀርፍ ያእ/الياء ለነስብ ምልከት ሆኗል። [وعلامة نصبه الياء نيابة عن الفتحة]
☞ ለ) የጥንድ ስም/مثنى
ምሳሌ رَأيْتُ الرجلَينِ ብንል الرجلَينِ የጥንድ ስም/مثنى ስለሆነ በፈተሀ ምትክ በሀርፍ ያእ/الياء ለነስብ ምልክት ሆኗል። [وعلامة نصبه الياء المفتوح ما قبلها والمكسور ما بعدها نيابة عن الفتحة]
④ የአሊፍ ፊደል/ألف በፈተሀ ምትክ ለነስብ ምልክት የሚሆነው አንድ ቦታ ላይ ነው እሱም» አምስቱ ስሞች/أسماء الخمسة ላይ።
ምሳሌ رَأيتُ أباكَ ብንል أباكَ ከአምስቱ ስሞች/أسماء الخمسة አንዱ ስለሆነ በፈተሀ ምትክ በአሊፍ/الف ለነስብ ምልክት ሆኗል።
[وعلامة نصبه الألف نيابة عن الفتحة]
⑤ የኑን ፊደል መውደቅ/حذف النون በፈተሀ ምትክ ለነስብ ምልክት የሚሆነው አንድ ቦታ ላይ ነው እሱም» አምስቱ ግሶች/ أفعال الخمسة ላይ።
ምሳሌ لَنْ يَضْرِبُوا ብንል يَضْرِبُوا ከአምስቱ ግሶች/أفعال الخمسة አንዱ ስለሆነ በፈተሀ ምትክ የኑን ፊደል መውደቅ/ حذف النون ለነስብ ምልክት ሆኗል።


==========
✔የኸፍድ ምልክቶች…(علامات الخفض) ክፍል 3
* ኸፍድ/خفض ፣ ጀር/جر ወይም ከስራ/كسرة ትርጉማቸው አንድ ነው፤ ኸፍድ የረፍአዕ ተቃራኒ ሲሆን ከታች ማለት ነው፤ ሀረካውም የሚቀመጠው ከፊደል በታች ነው። የቃሉ የመጨረሻ ፊደል ከስራ/ቂፍዳ ሲሆን ደግሞ መኽፉድ/مخفوض ወይም መጅሩር/مجرور ይባላል።
* ኸፍድ 3 ምልክቶቸ አሉት ① ዋና (أصل) ምልክቱ ከስራ/كسرة ሲሆን ሌሎችም ከስራን ተክተው የሚመጡ 2 ምልክቶች አሉት ② ፈትሀ/فتحة እና ያእ/الياء ናቸው።
① ከስራ/كسرة ለኸፍድ/خفض ምልክት የሚሆነው 3 ቦታ ላይ ነው።
ሀ) ነጠላ ስም/اسم مفرد
ለ) ወጥ-ያልሆነ የወንድ ብዙ ቁጥር/جمع تكسير
ሐ) ወጥ-የሆነ የሴት ብዙ ቁጥር/جمع مؤنث سالم ናቸው።
☞ሀ) ነጠላ ስም/اسم مفرد
ምሳሌ ٍمَرَرْتُ بِرَجُل ብንል رَجُلٍ ያለው ነጠላ ስም/اسم مفرد ስለሆነ በግልፅ ከስራ/كسرة ظاهرة ለኸፍድ ምልክት ሆኗል።
☞ለ) ወጥ-ያልሆነ የወንድ ብዙ ቁጥር/جمع تكسير
ምሳሌ مَرَرْتُ بِالرِّجال ብንል الرِّجال ያለው ወጥ-ያልሆነ የወንድ ብዙ ቁጥር/جمع تكسير ስለሆነ በግልፅ ከስራ/كسرة ظاهرة ለኸፍድ ምልክት ሆኗል።
☞ሐ) ወጥ-የሆነ የሴት ብዙ ቁጥር/جمع مؤنث سالم
ምሳሌ مَرَرْتُ بِالمُؤمِناتِ ብንል المُؤمِناتِ ወጥ-የሆነ የሴት ብዙ ቁጥር/جمع مؤنث سالم ስለሆነ በግልፅ ከስራ/كسرة ظاهرة ለኸፍድ ምልክት ሆኗል።
② ፈትሀ/فتحة ለኸፍድ/خفض ምልክት የሚሆነው አንድ ቦታ ላይ ነው።
ሀ) የማይለወጥ ስም/اسم لاينصرف
ለምሳሌ مَرَرْتُ بِيُوسُفَ ብንል يُوسُفَ የሚለው የማይለወጥ ስም/اسم لاينصرف ስለሆነ በከስራ/كسرة ምትክ/نيابة በፈትሀ/فتحة ለኸፍድ/خفض ምልክት ሆኗል። መሆን የነበረበት የከስራ ምልክት/كسرة ነበር ነገር ግን ይህ ስሙ በተፈጥሯቸው ከማይለወጡ ወይም ከስራ መሆን ከማይችሉ ስሞች/اسم لاينصرف አንዱ ስለሆነ ነው በፈተሀ የተከሰረው።
③ ያእ/الياء ለኸፍድ/خفض ምልክት የሚሆነው 2 ቦታ ላይ ነው።
☞ ሀ) ወጥ-የሆነ የወንድ ብዙ ቁጥር/جمع مذكر سالم
ምሳሌ مَرَرْتُ بِالمُؤمِنِينَ ብንል المُؤمِنِينَ የሚለው ወጥ-የሆነ የወንድ ብዙ ቁጥር/جمع مذكر سالم ስለሆነ በከስራ/كسرة ምትክ/نيابة በያእ/الياء ለኸፍድ/خفض ምልክት ሆኗል።
* እዚህ ላይ የከስራው ምልክት ኑን/نون ሳይሆን ከኑን በፊት ያለው የያእ (ي) ሀርፍ ነው።
[وَعَلامَةُ خَفْضِهِ الياءُ المَكْسُور ما قَبْلَها والمَفْتُوح ما بَعْدَها نِيابَةً عَن الكَسْرَةِ]
☞ለ) ጥንድ ስም/تثنية أسماء ወይምمثنى ይባላል።
ምሳሌ ِمَرَرْتُ بِرَجُلَين ብንል ِ رَجُلَين ጥንድ ስም/تثنية أسماء ስለሆነ በከስራ/كسرة ምትክ/نيابة በያእ/الياء ለኸፍድ/خفض ምልክት ሆኗል። እዚህም ላይ የከስራው ምልክት ኑን/نون ሳይሆን ከኑን በፊት ያለው የያእ (ي) ሀርፍ ነው።
[وَعَلامَةُ خَفْضِهِ الياءُ المَفْتُوح ما قَبْلَها والمَكْسُور ما بَعْدَها نِيابَةً عَن الكَسْرَةِ]
==========
✔የጀዝም ምልክቶች… (علامات الجزم) ክፍል 4
* ጀዝም/جزم አራተኛው የኢዕራብ አይነት ሲሆን የአንድ ቃል የመጨረሻ ፊደል ስኩን/سكن (ሳድስ) ከሆነ ቃሉ መጅዙም/مجزوم ነው ይባላል። ስኩን ደግሞ የሀረካ ተቃራኒ ስለሆነ አንድ ቃል ሙተሀሪክ/متحرك ነው ከተባለ ስኩን አይደለም ማለት ነው። ጀዝም/جزم ሁለት ምልክቶች አሉት።
① ስኩን/سكن እና ② የሀርፍ መውደቅ/حذف حرف
* [የሚወድቁት ፈደሎች ሁለት አይነት ናቸው [ደካማ ፈደል/حرف علة እና የኑን ፊደል/نون] ናቸው።
♦① ዋናው (أصل) የጀዝም ምልክት ስኩን/سكن ሲሆን ሌሎች ስኩንን ተክተው/نيابة የሚመጡ ቅርንጫፍ ምልክቶችም አሉት "የሀርፍ መውደቅ/حذف حرف" ይባላል።
* ስኩን/سكن ለጅዝም ምልክት የሚሆነው አንድ ቦታ ላይ ነው»
☞ሀ) ጤነኛ የሆነ የወደ ፉት ግስ/فعل المضارع الصحيح
ምሳሌ لم يلدْ ብንል يلدْ የሚለው فعل مضارع ስለሆነ በግልፅ የስኩን ምልክት (ْ) ጀዝም ሆኗል።
♦② የሀርፍ መውደቅ/حذف حرف
* የሀርፍ መውደቅ/حذف حرف ለጀዝም ምልክት የሚሆነው 2
ቦታ ላይ ነው።
☞ሀ) ጤነኛ ያልሆነ የወደፊት ግስ/فعل المضارع المعتل
ምሳሌ لم تر ብንል تر ያለው أصل/መሰረቱ ترى ነበር አሊፍ መቅሱራ ወደቃ ነው። ስለዚህ ترى የሚለው فعل المضارع المعتل ስለሆነ በሀርፍ መውደቅ/حذف حرف ለጀዝም ምልክት ሆኗል። وَعَلامَةُ جَزْمِهِ حَذْفُ حَرْفٍ نِيابَةً عَن السُكون]
☞ለ) 5ቱ ግሶች/أفعال خمسة
* ባለፈው የተዘረዘሩት 5ቱ ግሶች ረፍዕ/رفع የሚሆኑት በኑን መገኘት/ثبوت النون ሲሆን ጀዝም የሚሆኑት ደግሞ ኑኑን በመጣል/حذف النون ይሆናል።
ምሳሌ ረፍዕ የነበረውን يضربون ወደ لم يضربوا ብንቀይረው ጀዝም ሆነ ማለት ነው። ስለዚህ يدخلون ከ5ቱ ግሶች አንዱ ስለሆነ የኑን ፊደልን በመጣል/حذف النون ለጀዝም ምልክት ሆኗል። * [وَعَلامَةُ جَزْمِهِ حَذْفُ نُونِ نِيابَةً عَن السُكون]


-----------------------
ጃርና መጅሩር (جَار مَجْرُور) ጎታችና ተጎታች ምሳሌ
==============✔የሁሉም የኢዕራብ ክፍሎች ማጠቃለያና ጥያቄዎች…?
* እያንዳንዱ ቁጥርና ፊደል የሚወክለውን ከምስሉ ላይ በማየት እነዚህን 43 ባዶ ቦታዎች ሙሉ።
1……?
2……?
3……?
4……?
1a……?
1b……?
1c……?
1d……?
2a......?
2b......?
2c......?
2d......?
2e......?
3a......?
3b......?
3c......?
4a......?
4b......?
1aሀ……?
1aለ……?
1aሐ……?
1aመ……?
1bሀ……?
1bለ……?
1cሀ……?
1dሀ……?
2aሀ……?
2aለ……?
2aሐ……?
2bሀ……?
2cሀ……?
2cለ……?
2dሀ……?
2eሀ……?
3aሀ……?
3aለ……?
3aሐ……?
3bሀ……?
3cሀ……?
3cለ……?
4aሀ……?
4bሀ……?
4bለ……?
=============
✔ኢዕራብ (إعراب) ማለት ምንድነው…?
* የአንድ ቃል የመጨረሻው ፊደል ከሗላው በሚመጡ ነገሮች ምክንያት በግልፅም ይሁን በድብቅ ሁኔታው ሲቀያየር ኢዕራብ (اعراب) ይባላል። ለምሳሌ "الله" የሚለው ቃል ረፍእ የሚያደርግ ሲመጣበት ረፍእ ሲሆን (أَنا اللهُ) ነስብ የሚያደርግ ሲመጣበት ነስብ ሲሆን (إنَّ اللهَ) ኸፍድ/ከስራ የሚያደርግ ሲመጣበት ኸፍድ ሲሆን (بِاللهِ) ከታች በምስሉ ላይ በደንብ ይታያል። "يخرج" የሚለውም ምሳሌ እንደዚያው ከፊት በሚገቡ ነገሮች ሁኔታው ሲቀያየር ከታች በምስሉ ላይ ይታያል።
* ኢዕራብ (اعراب) በ 4 ይከፈላል» ረፍዕ፣ ነስብ፣ ኸፍድና ጀዝም (رَفْعٌ، نَصْبٌ، خَفْضٌ، جَزْمٌ) ከእነዚህ 4ቱ ደግሞ
* ስም/اسم የምንለው» ረፍእ፣ ነስብና ኸፍድ መሆን ሲችል ጀዝም/ስኩን መሆን ግን አይችልም፤ ማለትም ስም የሆነ ነገር የመጨረሻው ፊደል ስኩን አይሆንም (የናህው ህግ ነው)።
* ግስ/فعل የምነለው» ረፍእ፣ ነስብና ጀዝም መሆን ሲችል ኸፍድ/ከስራ መሆን ግን አይችልም፣ ማለትም የግስ/فعل የመጨረሻ ፊደል ከስራ አይሆንም (የናህው ህግ ነው)
* ከዚህ በመነሳት አንድ ቃል በ4ቱም የኢዕራብ አይነቶች መለዋወጥ ሲችል ሙዕረብ (معرب) ይባላል። እነሱም በ2 ይከፈላሉ (معرب بالحروف ومعرب بالحركات) ለምሳሌ ከታች ያሉት 2 ምስሎች የሙዕረብ (የሚለዋወጡ) ምሳሌዎች ናቸው። እሱ ይወጣል (هو يخرجُ) የሚለው ሲተዓረብ»
["يخرجُ" خبر مرفوع وعلامة رفعه ضمة]
* ከአራቱ በአንደኛው አይነት ላይ ብቻ ተገድቦ ሲገነባ መብንይ (مبني) ይባላል።
* ለምሳሌ አብዛሀኞዎቹ ፊደላት (حروف) የሚቀያየሩ አይደሉም በረፍእ፣ በነስብ፣ በኸፍድ ወይም በስኩን በአንዱ ላይ ብቻ መብንይ (የተገነቡ) ናቸው። ለምሳሌ (لمْ) የሚለውን ፊደል ብናይ መጨረሻው ሁልጊዜ በስኩን ላይ መብንይ (የማይለዋወጥ) ነው። (مبني على السكون لا محل له)።

=================
የግስ ግንባታና ሁኔታ...(بناء الفعل وإعرابه) ክፍል-1
* ግስفعل ሶስት ነገር (ረፍዕرفع ፣ ነስብنصب እና ጀዝምجزم) መሆን ሲችል 4ተኛ (ኸፍድخفض) መሆን ግን አይችልም።
* የ3ቱንም የግስ/فعل አይነት ቢናእና ኢዕራብ ከፋፍለን እንይ»
♦① {ያለፈ ጊዜ ግስ/بناء فعل المضي}
* ግንባታው በ3 ሁኔታዎች ይከፈላል፡
✔ሀ)የግሱ የመጨረሻው ፊደል صحيح ከሆነ በግልፅ/ظاهر ፈተሀ/فتحة መፍቱህ ይሆናል።
☞ምሳሌ َضَرَب ስንል የግሱ የመጨረሻ ፊደል "ፈትሀ/فتحة" ስለሆነ ግሱ صحيح ነው ስለሆነም በግልፅ መፍቱህ ነው። (مبني على الفتح الظاهر)
✔ለ) የግሱ የመጨረሻው ፊደል ሙዕተልمعتل ከሆነ ኢዕራቡ በውስጥ/تقدير መፍቱህ ይሆናል።
ምሳሌ هَدَى ስንል የግሱ የመጨረሻ ፈደል (ي) ደካማ/ሙዕተልمعتل ስለሆነና ፈትሀው በግልፅ ስለማይታይ ኢዕራቡ "በውስጥ ፈትሀ የተገነባ (مبني على الفتح المقدر) ይባላል።
✔ሐ) የግሱ የመጨረሻ ፊደል በተውላጠ-ስም ቅጥያ (ضمير) ከተያዘ ከዶሚሩ ፊደል በፊት ባለው ሁኔታ መብንይمبني ይሆናል ይህም ማለት በ3 መልክ ይታያል ማለት ነው።
[ዶማ ከሆነ በዶማ፤ ፈተሀ ከሆነ በፈተሀ፣ ስኩን ከሆነ በስኩን]
☞ሀ) በዶም ላይ መብንይ የሆነ/مبنيٌّ على الضمّ
ምሳ፡ ضَرَبُو) مبني على الضم)
☞ለ) በፈትሀ ላይ መብንይ የሆነ/مبني على الفتح
ምሳ፡ ضَرَبَا) مبني على الفتح)
☞ሐ) በስኩን ላይ መብንይ የሆነ/مبنيٌّ على السكون
ምሳ፡ ضَرَبْتُ) مبني على السكون)
---------------------
የግስ ግንባታና ሁኔታ...(بناء الفعل وإعرابه) ክፍል-2
♦② የወደፊት ጊዜ ግስ/فعل مضارع
* የሙዷሪእ ግስ/مضارع የሚጀምረው በ أَنَيْتَ ፊደሎች ሲሆን የሚጨርሰው ደግሞ በረፍእ (ዶማ) ነው። የأَنَيْتَ ፊደሎች የሚባሉት፡ ሀምዛ (أَ)፣ ኑን(ن) ፣ ያእ (ي) እና ታእ (ت) ናቸው። ምሳሌ፡ (أَضْرِبُ ، نَضْرِبُ ، يَضْرِبُ ، تَضْرِبُ)
* የሙዷሪእ ግስ ኢዕራብ በ 2 መልክ ይታያል»
✔1) ከግሱ በፊት የሚነስብ ወይም የሚጀዝም ፊደል ካልገባበት ሁልጊዜ መርፉዕ/مرفوع ነው።
☞ምሳሌ1 يَضْرِبُ ስንል ከግሱ በፊት የሚነስብ ወይም የሚጀዝም ስላልገባበት (لتجرده من الناصب والجازم) ኢዕራቡ መርፉዕ/مرفوع ነው። የመርፉእነት ምልክቱም የግሱ የመጨረሻ ፊደል ግልፅ "ዶማ" ሆኗል።
✔2) ከግሱ በፊት የሚነስብ ወይም የሚጀዝም ፊደል ሲገባበት
* በ2 መልክ ይታያል»
☞ሀ) ከግሱ በፊት የሚነስብ ፊደል ሲገባ
ምሳሌ፡ َلن يضرب ስንል ከግሱ በፊት የሚነስብ ፊደል ስለገባበት ኢዕራቡ መንሱብ/منصوب ይሆናል። የመንሱብነት ምልክቱም የግሱ መጨረሻ ፊደል ግልፅ "ፈተሀ" ሆኗል።
* የሙዷሪዕነ ግስን የሚነሰቡ ፊደሎች/نواصب ብዛት 10 ነው፡
[أَنْ، لَنْ، إِذَنْ، كَيْ، لَامُ كَيْ، لَامُ اَلْجُحُودِ، حَتَّى، الْجَوَابُ بِالْفَاءِ، الْوَاوِ، أَوْ]
☞ለ) ከግሱ በፊት የሚጀዝም ፊደል ሲገባ
ምሳሌ2፡ ْلم يضرب ስንል ከግሱ በፊት የሚጀዝም ፊደል ስለገባበት ኢዕራቡ መጅዙም/مجزوم ሆኗል። የጀዝምነት ምልክቱም የግሱ መጨረሻ ፊደል ግልፅ "ስኩን" ሆኗል።
* የሙዷሪዕ ግስን የሚጀዝሙ ፊደሎች/جوازم ብዛት 18 ነው፡
፡ [لَمْ، لَمَّا، أَلَمْ، أَلَمَّا، لَامُ اَلْأَمْرِ الدُّعَاءِ، "لَا" فِي اَلنَّهْيِ وَالدُّعَاءِ، إِنْ, مَا ، مَنْ ، مَهْمَا، إِذْمَا ، أي مَتَى، أَيْنَ ، أَيَّانَ، أَنَّى ، حَيْثُمَا ، كَيْفَمَا ، إِذًا فِي اَلشِّعْرِ خاصة]
♦③ {ተእዛዛዊ ግስ/فعل أمر }
* ተእዛዛዊ ግስ/فعل أمر ሁልጊዜ መጅዙም ነው/مبني على السكون ይህም በ 2 መልክ ይታያል»
☞ሀ) የግሱ መጨረሻ በግልፅ ስኩን/السكون الظاهرة መጅዙም ሲሆን፡
* ምሳሌ፡ إضْرِبْ ስንል የግሱ የመጨረሻ ፊደል "ስኩን" ስለሆነ ኢዕራቡ መጅዙም/مجزوم ነው።
☞ለ) የግሱ የመጨረሻ ፊደል ደካማ/حرف العلة ሲሆን ስኩንን በመተካት የፊደል መውደቅ/حذف حرف ምልክት ይሆናል።
* ምሳሌ፡ فَصَلِّ ስንል መሰረቱ فَصَلِّي ነበር ለጀዝምነት ምልክት ሲባል ያእ ፊደል (ي) ወድቃ ነው።
------------------------
✔5ቱ ድርጊት ተቀባዮች.. (مفاعيل الخمسة) ክፍል-2
* ከ15 መንሱባቾች ውስጥ 5ቱን መንሱባቶች በአንድ ስም "5ቱ ድርጊት ተቀባዮች" (مفاعيل الخمسة) ብለን በማሰጠር ቁጥሩን ወደ 10 መቀነስ ይቻላል። 5ቱ ድርጊት ተቀባዮች የሚባሉት፡-
① መፍዑል-ቢሂ (المفعول به)
② መፍዑል-ፊሂ (المفعول فيه)
③ መፍዑል-መዓሁ (المفعول معه)
④ መፍዑል-ለሁ (المفعول له)
⑤ መፍዑል-ሙጥለቅ (المفعول المطلق)
* እያንዳንዱን በጥልቀት እንይ፡
♦① መፍዑል-ቢሂ (المفعول به)
* ባለፈው ክፍል-1 ላይ በደንብ ታይቷል …
☞{ክፍል-2}
♦② መፍዑል-ፊሂ (المفعول فيه) ክፍል-2
* በውስጡ ድርጊት የተፈፀመበት ወይም የተሰራበት ወቅት ወይም ቦታ የሚገልፅ ስም "መፍዑል-ፊሂ (مفعول فيه) ይባላል። እሱም በ2 ይከፈላል፡
✔①፡ዞርፉ-ዘማን ظرف الزمان (የወቅት ስም)
* በውስጡ ድርጊት የተፈፀመበትን ጊዜ ወይም ወቅት የሚገልፅ ስም ነው። ህጉ (حكم) ሁልጊዜ መንሱብ (منصوب) ነው። * ዞርፉ ዘማን የሚባሉት፡
[الْيَوْم، وَاللَّيْلَة، وَغَدْوَةً، وَبُكْرَةً، وَسَحَرًا، وَغَدًا، وَعَتَمَةً، وَصَبَاحًا، وَمَسَاءً، وَأَبَدًا، وَأَمَدًا]
☞ምሳሌ፡ سافر زيدٌ اليومَ ብንል اليومَ የሚለው ዞርፉ-ዘማን ስለሆነ መጨረሻው መንሱብ (ፈተሀ) ሆኗል።
✔②፡ዞርፉ-ልመካን ظرف المكان (የቦታ ስም)
* በውስጡ ድርጊት የተፈፀመበትን ቦታ የሚገልፅ ስም ነው። ህጉ (حكم) ሁልጊዜ መንሱብ (منصوب) ነው። * ዞርፉ-ዘማን የሚባሉት፡
[أَمَامَ، وَخَلْفَ، وَقُدَّامَ، وَوَرَاءَ، وَفَوْقَ، وَتَحْتَ، وَعِنْدَ، وَمَعَ، وَإِزَاءَ، وَحِذَاءَ، وَتِلْقَاءَ، وَثَمَّ، وَهُنَا]
☞ምሳሌ፡. جَلَسَ الطَّالِبُ أمَامَ الْمُعَلِّمِ ስንል أمَامَ የሚለው ዞርፉ-ልመካን ስለሆነ መጨረሻው መንሱብ (ፈተሀ) ሆኗል።
☞ማስታወሻ፡
* 5ቱ የሚባል ነገር ቢበዛም ናህውን ለማቅለል ታስቦ ነው። እስኪ እናስታውሳቸው»
①፡ 5ቱ ስሞች (أسماء الخمسة) ፡
[ابوك، اخوك،حموك، ذو مال، فوك]
②፡ 5ቱ ግሶች (أفعال الخمسة) ፡
[ يضربون، تضربون، يضربان، تضربان، تضربين]
③፡ 5ቱ ድርጊት ተቀባዮች (مفاعيل الخمسة)፡
፡ [مفعول به, مفعول فيه, مفعول معه، مفعول له، مفعول مطلق]
-------------------------
✔መፍዑል-መዓሁ… (ُمَفْعُول مَعَه) ክፍል-3
* ከዋናው ፋዒል (የዓ.ነገር ባለቤት) ጋር በተግባር ሳይጋራ አብሮነትን ወይም ጓደኝነትን ለመግለፅ የሚመጣ ስም መፍዑል-መዓሁ (ُمَفْعُول مَعَه) ይባላል፤ ከ5ቱ ድርጊት ተቀባዮች (ِمَفَاعِيلُ الخَمْسَة) አንዱ ነው።
* ይህ ስም ለዓጥፍعطف ወይም ለማያያዝ ባልመጣች የዋው (واو) ፊደል ጋር የምሚጣ ሲሆን ህጉም እንደ ሌሎቹ መፋዒሎች መንሱብ ነው። በዚህ ክፍል 2 አይነት ዋው (واو) እናያለን።
① የዓጥፍ ዋው (واو العطف) እና
② ዋውል መዒያህ (واو المعية)
✔ ① የዓጥፍ ዋው (واو العطف)
* በትክክል ተግባርን ወይም ስራን ለማቆራኘት ወይም ዓጥፍንعطف ለመግለፅ የምትመጣ ዋው (واو) ናት።
☞ምሳሌ: َسَارَ زيدٌ وَمحمدٌ ስንል محمدٌ ዘይድንزيدን ተከትሎ ስለመጣ ዓጥፍ ነው። ይህ ማለት ዘይድና ሙሀመድ አብሮነትን ለመግለፅ ብቻ ሳይሆን በትክክል መሄድን ተጋርተዋል ወይም ሁለቱም ሂደዋል ማለት ነው።
✔② ዋውል መዒያህ (واو المعية)
* አብሮነትን ለመግለፅ እንጂ በትክክል ተግባርን ወይም ስራን ለማቆራኘት ወይም ዓጥፍንعطف ለመግለፅ የምትመጣ ዋው (واو) አይደለችም። ዋውል መዒያህ (واو المعية) መሆኑ የሚታወቀውም አንዱ ትርጉም የሚያበላሽ ወይም ከተጨባጭ አውነት ጋር የማይሄድ ሲሆን።
☞ምሳሌ1፡ َسَارَ زيدٌ وَالْقَمَر ብንል القمرَ መፍዑል-መዓሁ (مفعول معه) ስለሆነ መንሱብ ሆናል። ማለትም ጨረቃና ዘይድ ተግባርን (ስራን) አይጋሩም ምክንያቱም ጨረቃ ከዘይድ ጋር በተጨባጭ እየሄደች ሳይሆን አብሮነቱን ለመግለፅ ብቻ ነው። ዘይድ በትትከል እየተራመድ ሲሂድ ጨረቃም አብራው (معه) ትሄዳለች ለማለት ያህል ነው።
--------------------------- ✔5ቱ ድርጊት ተቀባዮች (مفاعيل الخمسة) ክፍል-4 እና 5
♦መፍዑል-ሊአጅሊሂ (مَفْعُول لِأجْلِهِ) ክፍል - 4
* የሆነን ነገር ፈልገን የሰራን መሆኑን በምክንያት ለመግለፅ የምነጠቀመው ስም መፍዑል-ሊአጅሊሂ (مَفْعُول لِأجْلِهِ) ወይም መፍዑል-ለሁ (مَفْعُول لَهُ) ይባላል። በሌላ አገላለፅ መፍዑል-ለሁ "ለምን..?" (لِمَاذَا) የሚልን ጥያቄ የሚመልስ ስም ነው። እንደሌሎቹ 5 መፍዑሎች ህጉ (حكم) መንሱብ ነው።
ምሳሌ፡ صَلَّيْتُ طَاعَةً لِله (አሏህን ለመታዘዝ ሶላት ሰገድኩ) ብንል "طَاعَةً" ያለው መፍዑል-ለሁ (مَفْعُول لَهُ) ይባላል። "ለምን ትሰግዳለህ?" ብትባል አላህን ለመታዘዝ (طَاعَةً لِله) ብለህ ትመልሳለህ። ስለዚህ መፍዑል-ለሁ (مَفْعُول لَهُ) "ለምን..? ወይም " لِمَاذَا የሚለውን ጥያቄ መለሰ ማለት ነው።
✔ መፍዑል-ሙጥለቅ… (مَفْعُول مُطْلَق) ክፍል-5
* አንድን ነገር ወይም ተግባር አክብደን (توكيد) ለመግለፅ የምንጠቀመው 3ተኛው የግስ ድርደራ (ِتَصْرِيفُ الْفِعْل) ወይም ስረ-ወቃል (مَصْدَر) መፍዑል-ሙጥለቅ (مَفْعُول مُطْلَق) ይባላል። 3ተኛው የግስ ድርደራ (تصريف الفعل) ማለት ምሳሌ፡ ضَرَبَ يَضْرِبُ ضَرْبًا ስንል ضَرْبًا የሚለው በግስ ድርደራ 3ተኛ ላይ ነው ስለዚህ ይህ ስም ስረወ-ቃል (مَصْدَر) ይባላል ።
* መፍዑል-ሙጥለቅ (مَفْعُول مُطْلَق) በ2 ይከፈላል፡-
♦፡① لَفْظِيٌ (ንግራራዊ)፡- ስረ-ወቃሉ (مَصْدَر) ከግሱ ጋር በንግግር (لفظيٌ) ወይም በፊደል ከተመሳሰለ لفظيٌ (ንግራራዊ) ይባላል።
☞ምሳሌ፡ ضَرَبْتُهُ ضرباً (መምታትን መታሁት) ስንል ضرباً ያለው ስረ-ወቃል (مَصْدَر) ከግሱ ጋር በፊደልም በትርጉምም ስለተመሳሰሉ لَفْظِيٌ ነው።
♦፡② مَعْنَوِيٌ (ትርጉማዊ)፡- ስረ-ወቃሉ (مَصْدَر) ከግሱ ጋር በንግግር (لفظيٌ) ወይም በፊደል ሳይመሳሰል በትርጉም (مَعْنَى) ብቻ ከተመሳሰሉ مَعْنَوِيٌ (ትርጉማዊ) ይባላል።
☞ምሳሌ፡ جَلَسْتُ قُعُودًا (መቀመጥን ተቀመጥኩ) ስንል قُعُودًا ያለው ስረ-ወቃል (مَصْدَر) ከግሱ ጋር በትርጉም እንጂ በፊደል ስላልተመሳሰለ مَعْنَوِيٌ ነው ።

-------------------------------- ✔የስም አይነትና ሁኔታ …(أقسام الاسم واعرابه) ክፍል-1
* ግስفعل መርፉእ፣ መንሱብና መጅዙም መሆን እንደሚችል አይተናል አሁን ደግሞ የስምንاسم ኢዕራብ እናያለን። ስምاسم ከኢዕራብ ክፍሎች ረፍእ፣ ነስብና ኸፍድ መሆን ሲችል ጀዝም (ስኩን) መሆን ግን አይችልም። ስለዚህ ስም በ 3 ይከፈላል ① መርፉእمرفوع ② መንሱብمنصوب እና ③ መኸፉድمخفوض። ከነዚህ ውስጥ መርፉእمرفوع የሆኑት ብዛታቸው 7 ነው፤ መንሱብمنصوب የሆኑት ደግሞ 15 ሲሆን መኸፉድمخفوض የሆኑት 3 ብቻ ናቸው።
♦① መርፉእمرفوع የሚባሉት ስሞች (أسماء المرفوعات)
* የስሙ የመጨረሻ ፊደል በናህው ህግ ረፍእ (ዶማ) የሆነ፡
1)ሙብተዳእ/مبتدأ
2) ኸበር/خبر
3) ፋኢል/ فاعل
4) ናኢበል ፋኢል/ناءب الفاعل
5) ኢስሙ ካነ/اسم كان
6) ኸበሩ ኢንነ/ خبر إنّ
7) አታቢዑ/التبع
♦② መንሱብمنصوب የሚባሉት ስሞች (أسماء المنصوبات)
* የስሙ የመጨረሻ ፊደል በናህው ህግ ነስብ (ፈተሀ) የሆነ፡
1) ኢስሙ አንነ/اسم إنَّ
2) ኸበሩ ካነ/خبر كان
3) አኸዋቱ ካነ/ኢንነ (أخوات كان/أن)
4) ኢስሙ ላ/اسم لا
5) ሙናዳ/المنادى
6) ሙስተስና/المستثنى
7) ተምይዝ/التميز
8) ሃል/الحال
9) መስዶር/المثدر
10) መፍኡል መዓሁ/المفعل مه
11) መፍኡል ቢሂ/المفعول به
12) መፍኡል ለሁ/المفعول له
13) ዞርፉ ዘማን/الظرف الزمان
14) ዞርፉል መካን/الظرف المكان
15) አታቢዑ/التبابع
♦③ መኸፉድمخفوض የሚባሉት ስሞች (أسماء المخفضات)
* የስሙ የመጨረሻ ፊደል በናህው ህግ ኸፍድ (ከስራ) የሆነ፡
1) መኽፉድ ቢል ሀርፍ/المخفوض بالحرف
2) መኽፉድ ቢል ኢዷፋ/المخفوض بالاضافة
3) አታቢዑ/التابع
☞ ይህን ሁሉ መሀፈዝ ስለሚከብድ በትሪያንግል ቅርፅ 3 ቦታ በመክፈል ማሳጠር ይቻላል። ከታች ያለው ምስል ይናገራል።
[مرفوعات]
① مبتدأ وخبر
② فاعل ونائب الفاعل
③ اسم كان وخبر إنّ
[منصوبات]
① اسم لا وإنّ وخبر كان
② مستثنى ومنادى
③ تمييز وحال
④ مفاعيل الخمسة
[مخفوضات]
① مخفوض بالحرف
② مخفوض بالاضافة
* التابع يتبع متبوعه
---------------------------- ✔የሐምዛና የመሳቢያ ፊደሎች ዝምድና… (ክፍል - 1)
* በተጅዊድ ህግ በአንድ ቃል ላይ ከሀምዛ ፊደል (ء) በፊት የመሳቢያ ፊደሎች (ا و ى) ከመጡ መሳቢያውን በደንብ አድርጎ መሳብ ዋጂብ ነው። ለምሳሌ (َجآء) የሚለውን ብናይ በአንድ ቃል ላይ ከሐምዛ በፊት አሊፍ መሳቢያ መጥቷል ስለዚህ የመድ ምልክቱ ቢኖርም ባይኖርም እስከ 5 ሀረካ በደንብ አድርጎ መሳብ ዋጂብ/ ግዴታ ነው (مد الواجب)።
* ቁርአን ውስጥ በብዛት የምናገኘው የሐምዛንና የአሊፍን መገናኘት ቢሆንም ዋው (و) እና ያእም (ي) እንደዚሁ ከሐምዛ በፊት ሲመጡ እስከ 5 ሀረካ በደንብ አድርጎ መሳብና መቅራት ዋጂብ ነው። ከታች ምስሉ ላይ ያለውን 3 ምሳሌ ተመልከቱት።
-------------------------
✔የሐምዛና የመሳቢያ ፊደሎች ዝምድና… (ክፍል-2)
* የሐምዛ (أ) እና የመሳቢያ ፊደሎች (ا و ي) ተከታትለውና ተራርቀው ሲመጡ እንደ መዱልዋጂብ (በአንድ ቃል ላይ ተጠጋግተው እንደመጡት) መዱን እስከ 5 ሀረካ ማስረዘም ግዴታ አይደለም በ 2 ሀረካ ማሳጠር ወይም እስከ 5 ሀረካ ማስረዘም ሁለቱም የተፈቀደ ነው (مد الجائز)።
* ለምሳሌ (يدآ أبي) የሚለውን ብናይ ሐምዛና አሊፍ ተከታትለው ይምጡ እንጂ በአንድ ቃል ላይ አይደሉም በሁለት የተለያዩ ቃላት ላይ ተራርቀው ተቀምጠዋል ስለዚህ በዚህ ሁኔታ መዱን 5 ሀረካ መሳብም አለመሳብም የተፈቀደ ነው። ልክ እንደዚሁ የቀሩትም የመሳቢያ ፊደሎች (ا እና و) ከሐምዛ ጋር ተከታትለውና በሁለት የተለያዩ ቃላት ላይ ተራርቀው ሲመጡ መዱን መሳብም አለመሳብም የተፈቀደ ነው። ከታች ያለው ምስል በደንብ ያብራራዋል።
------------------------- ✔የግስ ክፍሎች… (أقسام الفعل)
♦ጊዜን መሰረት በማድረግ ግስ/فعل በ3 ይከፈላል፡
① ያለፈ ጊዜ ግስ/فعل ماض
② የአሁን ወይም የወደፊት ጊዜ ግስ/فعل مضارع
③ ትእዛዛዊ ግስ/فعل أمر
ምሳሌ ① ضَرَب/መታ ② ُيَضرِب /ይመታል ③ إضرِبْ/ምታ
♦የመጨረሻውን የፊደል አይነት በማየት ግስ በ 2 ይከፈላል፡
① ደካማ ግስ/معتل الآخر እና
② ጠንካራ ግስ/صحيح الأخر
* አሊፍ፣ ዋውና ያእ/ا و ي ደካማ ፊደል/حرف معتل ይባላሉ። እነዚህ ፊደሎች የግሱ መጨረሻ ላይ ካሉ ደካማ ግስ/فعل معتل ይባላል። ምሳሌ دعا፡ أرى፡ يدعو፡ يرصي
* የግሱ የመጨረሻ ፊደል ኖርማል ከሆነ ወይም ከላይ ከተጠቀሱት 3 ፊደሎች ውጭ ከሆነ ጠንካራ ግስ/فعل صحيح ይባላል። ምሳሌ ضرب ـ خرج
♦አድራጊንና ተደራጊን/subjuct & object በማየት ግስ በ 2 ይከፈላል።
✔① ያደረገ/የፈፀመ ግስ (مبني للمعلوم)
ምሳ1☞ َضَرَب/መታ» Past Active Tense» فعل ماض مبني للمعلوم [ግሱ በፈተሀ/فتحة ይጀምራል]
ምሳ2 ☞يَضْرِبُ/ይመታል» future Active Tense» فعل مضارع مبني للمعلوم [ግሱ በፈተሀ/فتحة ይጀምራል]
✔② የተደረገ/የተፈፀመበት ግስ (مبني للمجهول)
ምሳ1☞ ُضُرِب/ተመታ» Past passive Tense» ግሱ በዶማ/ضمة ይጀምራል።فعل ماض مبني للمجهول
ምሳ2☞ ُيُضْرَب/ይመታል» Past passive Tense» ግሱ በዶማ/صمة ይጀምራል።فعل مضارع مبني للمجهول
---------------------------------- ✔ፋዒል (فاعل) ማለት ምንድነው…?
* ፋዒል (فاعل) ከግስ (فعل) በሗላ የሚመጣ ሰም ሲሆን ከ7ቱ መርፉዓት مرفوعات አንዱ ነው። فعل ማለት ድርጊት (ግስ) ሲሆን فاعل ማለት ደግሞ ድርጊት ፈፃሚ (ባለቤት) ወይም ድርጊትን ያስገኘ ማለት ነው። ምሳሌ፡ جاء محمد ብንል جاء ድርጊት ሲሆን "محمد" ባለቤት (ድርጊት ፈፃሚفاعل) ይሆናል። በናህው ህግ ከفاعل በፊትفعل ይቀድማል።
* ፋዒል (فاعل) በ2 ይከፈላል። ① ግልፅ/የሚታይ ባለቤት (ظاهر) ② ተውላጠ ስም (مضمر)
♦① ግልፅ ባለቤት (ظاهر) ምሳሌ፡ ከላይ የተቀስነው جاء محمد ስንል محمد ግልፅ ባለቤት/فاعل ظاهر ነው።
♦② ተውላጠ ስም (مضمر) ባለቤቱ በግልፅ ሳይታይ ሲቀር ወይም ግሱفعل ብቻውን ሲሆን ነው። ምሳሌ جاء መጣ ስንል ፋዒሉفاعل በውስጠ-ተዋቂነት (በضمير) አለ ሲወጣ "እሱهو" ይሆናል። [ والفاعل ضمير مستترفيه تقديره هو]
* እንደ ተውላጠ ስሙ/ضمير ሁኔታ ፋኢሉفاعل ይወሰናል ምሳሌ፡ ْضربت ከሆነ فاعل ፡ هي ይሆናል፤ ضربو ከሆነ فاعل ፡ هم ይሆናል። የሁሉም ዶሚሮች በዚህ መሰረት ይሆናል።
* በናህው 12 ተውላጠ ስሞች/ዶሚሮች (ضمير) አሉ፡
[ضَرَبْتُ، وَضَرَبْنَا، وَضَرَبْتَ، وَضَرَبْتِ، وَضَرَبْتُمَا، وَضَرَبْتُمْ، وَضَرَبْتُنَّ، وَضَرَبَ، وَضَرَبَتْ، وَضَرَبَا، وَضَرَبُوا، وضربن]
* ስለዚህ ፋኢል ህጉ መርፉእ ነው فاعل مرفوع
----------------------------- ✔የሙብተዳእ እና የኸበር ህግ ቀያሪዎች… ክፍል-4
፡ (عوامل الداخلة على المبتدأ والخبر)
* የሙብተዳእና የኸበርን ሁኔታ የሚለውጡ ነገሮች 3 ናቸው።
① ካነ (َكَان) እና እህቶቿ [كَانَ وَأَخَوَاتُهَا]
② ኢንነ (إنَّ) እና እህቶቿ [إِنَّ وَأَخَوَاتُهَا]
③ ዞነንቱ (ظَنَنْتُ) እና እህቶቿ [ظَنَنْتُ وَأَخَوَاتُهَا]
* የሙብተዳእና የኸበር ስም ላይ كَان ወይም إنَّ ቀድመው ሲገቡ ነባሩን ህግ (መርፉዕነቱን) ይለውጡታል። ምሳሌ»
♦የካነ ስምاسم كان እና የኢንነ ኸበር خَبَرُ إنَّ መርፉእ ናቸው።
✔የካነ ስም (اسم كان) ህጉ መርፉዕ (مرفوع)ነው።
☞ምሳሌ كَانَ اللهُ غَفُورًا ስንል اللهُ የሚለው የካነ ስምاسم كان ስለሆነ መርፉዕ ሆኗል። [غَفُورًا ኸበሩ ካነ خبر كان መንሱብ]
✔የኢንነ ኸበር (خَبَرُ إنَّ) ህጉ መርፉዕ (مرفوع)ነው።
☞ምሳሌ إنَّ اللهَ غَفُورٌ ስንል غَفُورٌ የሚለው የኢንነ ኸበር خبر إنَّ ስለሆነ መርፉዕ ሆኗል።
♦ማስታወሻ፡ የመንሱባት ክፍል (المنصوبات) ላይ የሚታዩ የكَان እና የإنَّ ህጎች»
✔የካነ ኸበር (َخَبَرُ كَان) ህጉ መንሱብ (منصوب) ነው።
☞ምሳሌ [غَفُورٌ የካነ ኸበር خَبَرُ كَان ስለሆነ መንሱብ ሆኗል]
✔የኢንነ ሰም (إسْمُ إنَّ) ህጉ መንሱብ (منصوب) ነው።
☞ምሳሌ [اللهَ የኢንነ ስም اسم إنَّ ስለሆነ መንሱብ ሆኗል]
♥ ለሌሎቹም የكَان እና የإنَّ ወንድሞች ህጋቸው በዚህ መሰረት መርፉዕ (مرفوع)ነው።።
♦፡የكَان እህቶች (أخواة كان)
☞፡ [أَمْسَى، أَصْبَحَ، أَضْحَى، ظَلَّ، بَاتَ، صَارَ، لَيْسَ، مَا زَالَ، مَا اِنْفَكَّ، مَا فَتِئَ، مَا بَرِحَ، مَا دَامَ، مَا تَصَرَّفَ مِنْهَا نَحْوَ كَانَ، وَيَكُونُ، كُنْ، أَصْبَحَ ، يُصْبِحُ ، أَصْبِحْ]
♦፡የإنَّ እህቶች (أخواة إنَّ)
☞፡ [إِنَّ، أَنَّ، لَكِنَّ، كَأَنَّ، لَيْتَ، لَعَلَّ]
--------------------- ✔የስም ምልክቶች (علامات الاسم)
* አንድ የአረበኛን ቃል ትርጉሙን ብናውቀውም ባናውቀውም ስም/اسم መሆኑን የምናውቅበትና ከግስ/فعل የምንለይበት 5 ምልክቶች አሉ።
① የቃሉ የመጨረሻ ፊደል ኸፍድ/ከስራ ከሆነ
② የቃሉ የመጨረሻ ፊደል ተንዊን (ሁለት ሀረካ) ከሆነ።
③ የቃሉ መጀመሪያ ላይ አሊፍና ላም (አል/ال) ከገባበት
④ የቃሉ መጀመሪያ ላይ የኸፍድ ፊደል/መስተዋድድ ከገባበት
[የኸፍድ ፊደል መስተዋድ/preposition የምንላቸው»
(ከ/من, ወደ/الى, ስለ/عن, ላይ/على, ውስጥ/في, ስንተ/َرُبّ, የባእ, የካፍና የላም ፊደል/ب ,ك ,ل)
* እነዚህ ፊደሎች አንድን ቃል ከፊት ቀድመው ከመጡ የቃሉ መጨረሻ ፊደል ኸፍድ/ከስራ ይሆናል ይህ ደግሞ ስም/اسم መሆኑን ይገልፃል።
* የመማያ ፊደሎችም/حرف القسم የኸፍድ (ከስራ የሚያደርጉ) ፊደሎች ናቸው (و ب ت)። አንድ ቃል በእነዚህ ፊደሎች ከጀመረ ስም/اسم መሆኑን ይገልፃል። ለምሳሌ (والله, بالله, تالله) ከሚለውን መሀላ ብናይ الله የሚለው ቃል ስም መሆኑን የመማያ ፊደሎቹ ይጠቁማሉ።
* ለምሳሌ ከታች ምስሉ ላይ ባሉት 2 አያት ውስጥ 3 ስም እና 6 የስም ምልክቶች ይገኛሉ። [وَالْعَصْرِ إِنَّ الْإِنْسَانَ لَفِي خُسْرٍ ]
✔በ عصر የሚለው ቃል ስም/اسم መሆኑን የሚገልፁ 3 ምልክቶች አሉ» ① የመሀላ ፊደል ገብቷል (و) ② አል/ال ገብቷል ③ የቃሉ መጨረሻ ፊደል ኸፍድ/ከስራ ሆኗል
✔በ انسان የሚለው ቃል ስም/اسم መሆኑን የሚገልፅ 1 ምልክት አለ» ① አል/ال ገብቷል
✔በ خسر የሚለው ቃል ስም/اسم መሆኑን የሚገልፁ 2 ምልክቶች አሉ» ① የከፈድ ፊደል (في) ገብቷል ② የቃሉ መጨረሻ ፎደል ተንዊን/ ሁለት ሀረካ ሆኗል።
------------------------- ✔የግስ ምልክቶች (علامات الفعل)
* ልክ እንደ ስም/اسم, ግስም/فعل የራሱ የሚታወቅበት ወይም
ከስም የሚለይበት 4 ምልክቶች አሉት። * ማንኛውንም የአረበኛ ቃል ትርጉሙን ባናውቀውም ግስ/فعل መሆኑን በእነዚህ ምልክቶች ማወቅ ይቻላል። እነሱም:-
① በቃሉ መጀመሪያ ላይ የ قدْ ፊደል/حرف መግባት
② በቃሉ መጀመሪያ ላይ የ س ፊደል/حرف መግባት
③ በቃሉ መጀመሪያ ላይ سوف የሚል ቃል መግባት
④ በቃሉ መጨረሻ ላይ እንስትን የምትገልፅ ስኩን ታእ (تْ) መግባት
* ከታች ምስሉ ላይ ያሉትን 4 ምሳሌዎች ብናይ»
ምሳ.① قد أفلح من تذكى
ምሳ.② سيصلىٰ نارا
ምሳ.③ سوف تعلمون
ምሳ.④ تبتْ يدا
① የቃሉ መጀመሪያ ላይ قد ፊደል/حرف ስለገባ أفلح የሚለው ግስ/فعل ነው።
② የቃሉ መጀመሪያ ላይ የس ፊደል/حرف ስለገባيصلى የሚለው ግስ/فعل ነው።
③ የቃሉ መጀመሪያ ላይ سوف ስለገባ تعلمون የሚለው ግስ/فعل ነው።
④ የቃሉ መጨረሻ ላይ እንስትን የምትገልፅ ስኩን ታእ (تْ) ስለገባች تبَّ የሚለው ግስ/ فعل ነው።
------------------------- ✔መፍዑል-ቢሂ… (مَفْعُول بِهِ) ምን ማለት ነው?
☞ ፊዕልفعل » ድርጊት ወይም ግስ ማለት ነው።
☞ ፋዒልفاعل » አድራጊ ወይም ድርጊት ፈፃሚ ማለት ነው።
☞መፍዑል-ቢሂمَفْعُول بِهِ » ተደራጊ ወይም ድርጊት ተቀባይ ወይም ድርጊት የሚያርፍበት ማለት ነው።
✔ መፍዑል-ቢሂمَفْعُول بِهِተደራጊ ከ15ቱ መንሱባቶች አንዱ ስለሆነ ህጉ (حكمه) መንሱብمنصوب ነው።
* ልክ እንደ ፋዒልفَاعِل መፍዑል-ቢሂምمَفْعُول بِهِ በ2 ይከፈላል
ⓐ ግልፅ (ظاهر) ተደራጊمَفْعُول بِهِ እና
ⓑ ተደራጊ ተውላጠ-ስም (ضَمِير مَفْعُول بِهِ)
ⓐ ግልፅ (ظاهر) ተደራጊمَفْعُول بِهِ ማለት በይፋ የሚታይ ተደራጊ ስም ማለት ነው። ምሳሌ፡ ضَرَبْتُ زَيْدًا ስንል زَيْدًا የሚለው ግልፅ (ظاهر) ተደራጊمَفْعُول بِهِ ነው።
[ግሱفعل፡ضَرَبِ ፤ ፋዒሉفاعل፡ እኔأَنا]
ⓑ ተደራጊ ተውላጠ-ስም (ضَمِير مَفْعُول بِهِ) ማለት በይፋ የማይታይ በተውላጠ ስም የተተካ ተደራጊمَفْعُول بِهِ ስም ነው።
* ይህም በ2 ይከፈላል
① የተቀጠለ ድርጊት ተቀባይ ተውላጠ-ስም(ضمير متصل )
② የተለየ ድርጊት ተቀባይ ተውላጠ-ስም (ضمير منفصل)
✔① [የተቀጠለمُتَصِل ተደራጊ ተውላጠ-ስምضمير]
♦1ኛ መደብ/ተናጋረ (مُتَكَلِّم) »
1፡ضَرَبَنِي (መታኝ) » እሱ እኔን መታኝ።
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» እኔأَنـا
2፡ضَرَبَنَا (መታን)
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» እኛنَحْنُ /إنَّا
♦2ተኛ መደብ/ሙኻጦብ (مُخَاطَب) » ከፊት ያለ አድማጭ
3፡ضَرَبَكَ (መታህ)
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» አንተأَنْتَ
4፡ضَرَبَكِ (መታሽ)
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» አንቺأَنْتِ
5፡ضَرَبَكُمَا (መታችሁ ለ 2 ሰው)
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» እናንተأَنْتُمَا
6፡ضَرَبَكُمْ (መታችሁ ከ2 በላይ)
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» እናንተْأَنْتُم
7፡ضَرَبَكُنَّ (መታችሁ ለብዙ ሴቶች)
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» እናንተ أنْتُنَّ
♦3ተኛ መደብ/ጋኢብ (غَائِب) » ሩቅ
8፡ضَرَبَهُ (መታው)
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» እሱهُوَ
9፡ضَرَبَهَا (መታት)
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» እሷهِيَ
10፡ضَرَبَهُمَا (መታቸው ለ2 ሰው )
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» እነርሱهُمَا
11፡ضَرَبَهُمْ (መታቸው ለብዙ)
* አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» እነርሱهُمَا
12፡ضَرَبَهُنَّ (መታቸው ለብዙ ሴቶች)
አድራጊفاعل » እርሱ(هُوَ) ፤ ተደራጊ(مَفْعُول بِهِ)» እነርሱهُنَّ
☞ 12ቱም ተውላጠ-ስም (ضَمَائِر) ላይ አድራጊው/ድረጊት ፈፃሚው እርሱ (هُوَ) ሲሆን ተደራጊው/ድርጊት ተቀባዩ (مَفْعُول بِهِ) ደግሞ 12 የተለያዩ የተውላጠ-ስም ቅጥያዎች (ضَمِي مُتَّصِل) ናቸው።
✔② [የተለየمُنْفَصِل ተደራጊمَفْعُول بِه ተውላጠ-ስምضمير]
♦1ኛ መደብ (مُتَكَلِّمْተናጋሪ) የተለየمُنْفَصِل ተደራጊمَفْعُول بِه
1፡ إِيَّايَ (እኔን)
2፡ إِيَّانَا (እኛን)
♦2ተኛ መደብ (مُخَاطَبአድማጭ) የተለየمُنْفَصِل ተደራጊمَفْعُول بِه
3፡ إِيَّاكَ (እንተን)
4፡ إِيَّاكِ (እንቺን)
5፡ إِيَّاكُمَا (እናንተን ለ2 ሰው)
6፡ إِيَّاكُمْ (እናንተን ለብዙ)
7፡ إِيَّاكُنَّ (እናንተን ለብዙ ሴቶች)
♦3ተኛ መደብ (غَائِبሩቅ) የተለየمُنْفَصِل ተደራጊمَفْعُول بِه
8፡ إِيَّاهُ (እሱን)
9፡ إِيَّاهَا (እሷን)
10፡ إِيَّاهُمَا (እነሱን ለ2 ሰው)
11፡ إِيَّاهُمْ (እነሱን ለብዙ)
12፡ إِيَّاهُنَّ (እነሱን ለብዙ ሴቶች)
------------------------
✔ናኢበል-ፋዒል (نائب الفاعل) ማለት ምንድነው?
* ፋዒልን (አድራጊን) ተክቶ የመጣ ወይም ባለቤቱ ያልተገለፀ ተደራጊ ስም "نائب الفاعل" ወይም "المفعول الذي لم يسم فاعله" ይባላል። ከ7ቱ መርፉዓቶች አንዱ ስለሆነ ሁክሙ ሁልጊዜ መርፉዕ ነው። [نائب فاعل مرفوع]
* የናኢበል-ፋኢል ግስ (مبني للمجهول) በሁለት መልክ ይታያል፡
♦ ከናኢበል-ፋኢል በፊት ያለው ግሰ ያለፈጊዜ (ماضي) ከሆነ ቃሉ የሚጀምረው በዱማ ሲሆን ከመጨረሻው ፊደል በፊት ያለው ፊደል ደግሞ ከስራ ይሆናል።
[فَإِنْ كَانَ اَلْفِعْلُ مَاضِيًا ضُمَّ أَوَّلُهُ وَكُسِرَ مَا قَبْلَ آخِرِهِ،]
ምሳሌ፡ ضُرِبَ زَيْدٌ "ዘይድ ተመታ" ስንል زيد ናኢበል-ፋኢል ነው
♦ ከናኢበል-ፋኢል በፊት ያለው ግሰ ያለፈጊዜ (مضارع) ከሆነ የመጀምረያው ፊደል ዱማ (ضمة) ሲሆን ከመጨረሻው ፊደል በፊት ያለው ደግሞ ፈተሀ (فتحة) ይሆናል።
[وَإِنْ كَانَ مُضَارِعًا ضُمَّ أَوَّلُهُ وَفُتِحَ مَا قَبْلَ آخِرِهِ]
ምሳሌ፡ يُضْرَبُ زَيْدٌ "ዘይድ ይመታል" ስንል زيد ናኢበል-ፋኢል ነው።
☞ ናኢበል-ፋኢልም (نائب الفاعل) እንደ ፋዒል (فاعل) በሁለት ይከፈላል፡
✔① ግልፅ (ظاهر) የሆነ
ምሳሌ፡ ضُرِبَ زَيْدٌ ወይም يُضْرَبُ زَيْدٌ ስንል ናኢበል-ፋኢሉ (زَيْدٌ) በግልፃል።
✔② ግልፅ ያልሆነ (ضمير) ወይም በውስጠ-ተዋቂነት ያለ ናኢበል-ፋኢል
ምሳሌ፡ ضُرِبَ ወይም يُضْرَبُ ስንል ናኢበል-ፋኢሉ (زَيْدٌ) በግልፅ አልተቀመጠም "እሱ" የሚል በውስጠ-ተዋቂነት ግን አለ። ["نائب فاعل ضمير مستتر فيه تقديره "هو ]
* ለሁሉም 12 ዶማኢሮች ህጉ በዚህ መሰረት ነው።
----------------------- ✔4ቱ ተከታዮች (التوابع) 7ተኛው መርፉዓት ክፍል -1
* 4ቱ ተከታዮች (التوابع) የሚባሉት፡
① በመግለፅ የተከተለ (النعت) "ገላጭ"
② በማያያዝ የተከተለ (العطف) "ልጥቅ"
③ በማክበድ የተከተለ (اَلتَّوْكِيدُ) "ግነት"
④ በምትክ የተከተለ (البدل) "ልውጫ"
* በ3ቱም የስም አይነቶች (መርፉዓት፣ መንሱባትና መኽፉዷት) 4ቱም ተከታዮች (التوابع) በአንድ ህግ ይስማማሉ እሱም»
☞ "ተከታይ አስከታዩን ይከተላል" "التابع يتبع منعوته"።
* ስለዚህ ተከታይና አስከታይ (التابع والمتبوع) በ4 ነገሮች ላይ ሁልጊዜ መስማማት አለባቸው።
1) በኢዕራብ (الرفع والنصب والجر)
2) በቁጥር (الإفراد والتثنية والجمع)
3) በፆታ (التذكير والتأنيث) እና
4) በመታወቅ ወይም በመለየት (التعريف والتنكير)
✔አስከታይ ረፍዕ (رفع) ከሆነ ተከታይም ረፍዕ (رفع) ይሆናል፤ ነስብ ከሆነም ነስብ ይሆናል፤ ኸፍድ ከሆነም ኸፍድ ይሆናል።
✔ መዕሪፋ (معرفة) ከሆነ መዕሪፋ ይሆናል።
✔ ነኪራ (نكرة) ከሆነ ነኪራ ይሆናል።
✔ ነጠላ (مفرد) ከሆነ ነጠላ ይሆናል።
✔ ጥንድ (مثنى) ከሆነ ጥንድ ይሆናል።
✔ ብዙ ቁጥር (جمع) ከሆነ ብዙ ቁጥር ይሆናል።
✔ የተባእት ፆታ (مذكر) ከሆነ ተባእት ይሆናል።
✔ የአንስታይ ፆታ (مؤنث) ከሆነ አንስታይ ይሆናል።
♦① ገላጭ… (النعت) ክፍል -1
* ስምን የሚገልፅ ነገር ሁሉ"ገላጭ" (النعت) ይባላል። ምሳሌ ቸር ሰው (رجل كريم)፣ ቆንጆ ልጅ (أمرأة جميلة) ብንል ቸር እና ቆንጆ (جميلة) የሚሉት የስም ገላጮች ኗቸው። * "ገላጭ" (النعت) ደግሞ ከ4ቱ ተከታዮች (التوابع) አንዱ ስለሆነ ህጉ ተመሳሳይ ነው ስለሆነም ገላጭ ተገላጭን ይከተላል (التابع يتبع منعوته) ይባላል።
ምሳ1፡ "قَامَ زَيْدٌ اَلْعَاقِلُ" ብንል زَيْدٌ ያለው ተገላጭ (منعوت) ሲሆን اَلْعَاقِلُ ያለው ደግሞ ገላጭ (نعت) ነው፤ ስለዚህ "زَيْدٌ" መርፉዕ ስለሆነ ገለጩም (اَلْعَاقِلُ) መርፉዕ ሆኗል።
ምሳ2፡ رَأَيْتُ زَيْدًا اَلْعَاقِلَ [፡اَلْعَاقِلَ መንሱም ገላጭ]
ምሳ3፡ مَرَرْتُ بِزَيْدٍ اَلْعَاقِلِ [፡ اَلْعَاقِلِ መጅሩር ገላጭ]
❥የታወቀ ወይም የተለየ ስም (المعرفة) በ5 ነገሮች ይገለፃል
① በተውላጠ ስመ (الاسْمُ الْمُضْمَرُ) ምሳሌ፡ أَنَا وَأَنْتَ
② በወል ስም (الاسْمُ الْعَلَمُ) ምሳሌ፡ زَيْدٌ وَمَكَّةُ
③ በአመልካች ስም (الاسْمُ الْمُبْهَمُ) ምሳሌ፡ هَذا وَهَذِهِ
④ አሊፍና ላም የገባበት ስም (الاسْمُ الَّذِي فِيهِ الألِفُ وَالَّلامُ) ምሳሌ፡ الرَّجُلُ وّالْغُلامُ
⑤ ከእነዚህ 4 ስሞች ጋር የተያያዘ ስም (مَا أُضِيفَ إِلَى وَاحِدٍ مِنْ هَذِهِ الأَرْبَعَةِ)
❥ አሊፍንና ላምን الን መቀበል የሚችል፤ ለሁሉም የሚሆን ያልተለየ ስም ነከራ (نكيرة) ይባላል። ምሳሌ፡ رجل ، وغلام
✔4ቱ ተከታዮች… (التوابع) ክፍል-2፣ 3 እና 4
♦② ዓጥፍ… (الْعَطْفُ)
* የአጥፍ (የማያያዢያ) ፊደሎች 10 ናቸው እነሱም፡- (اَلْوَاوُ، وَالْفَاءُ، وَثُمَّ، وَأَوْ، وَأَمْ، وَإِمَّا، وَبَلْ، وَلَا، وَلَكِنْ، وَحَتَّى) * ሁሉንም ፊዶች በአንድ
"وَلَاكِنْ بَلْحَتَّىٰ ثُمَّ أَوْف أَمْإِمَّا"
ብለን በመሰብሰብ በቀላሉ ማስታወስ ይቻላል።
☞ም1፡ قَامَ زَيْدٌ وَعَمْرٌو (ዘይድ ቆመ አምርም)
☞ም2፡ رَأَيْتُ زَيْدًا وَعَمْرًا (ዘይድን አሁት አምርንም)
☞ም3፡ مَرَرْتُ بِزَيْدٍ وَعَمْرٍو (በዘይድ ስር አለፍኩ በአምርም)
❥ ግስ በግስ ላይ ሲያያዝ (ሲተዓጦፍ)
☞ምሳሌ፡ زَيْدٌ لَمْ يَقُمْ وَلَمْ يَقْعُدْ ()፡
♦③ ተውኪድ… (اَلتَّوْكِيدُ)
* ተውኪድ (توكيد) ማለት አንድ የተገለፀ ስምን ለማክበድ ወይም ለማጠንከር የምንጠቀምበት ከ4ቱ ተከታዮች (توابع) አንዱ ክፍል ነው። ስለዚህ ህጋቸው አንድ ነው "ተከታይ አስከታዩን ይከተላል" "التابع يتبع متبوعه" ።
* ተውኪድን ለመግለፅ የምንጠቀማቸው የተለመዱ ቃላቶች እነዚህ ናቸው።
[اَلنَّفْسُ ، الْعَيْنُ ، كُلُ ، أَجْمَعُ ... أَكْتَعُ ، وَأَبْتَعُ ، وَأَبْصَعُ]
☞ም1፡ قَامَ زَيْدٌ نَفْسُهُ (ዘይድ እራሱ ቆመ) ስንል نَفْسُهُ የሚለው ተውኪድ (توكيد) ስለሆነ እንደ ዘይድ (مأكد) አሱም ረፍዕ ሆኗል።
☞ም2፡ رَأَيْتُ اَلْقَوْمَ كُلَّهُمْ (ህዝቡን ሁሉንም አየሁ) ስንል كُلَّهُمْ የሚለው ተውኪድ (توكيد) ስለሆነ እንደ اَلْقَوْمَ) አሱም ነስብ ሆኗል።
☞ም3፡ مَرَرْتُ بِالْقَوْمِ أَجْمَعِينَ (በህዝቡ በጠቅላለው ስር አለፍኩኝ) ስንል أَجْمَعِينَ ያለው ተውኪድ (توكيد) ስለሆነ እንደ الْقَوْمِ አሱም ኸፍድ ሆኗል።
♦④ በደል… (بدل)
፡ [إِذَا أُبْدِلَ اِسْمٌ مِنْ اِسْمٍ أَوْ فِعْلٌ مِنْ فِعْلٍ تَبِعَهُ فِي جَمِيعِ إِعْرَابِهِ] * ስም በስም ወይም ግስ በግስ ሲለወጥ ተለዋጩ ስም (بدل) አስለዋጩን ስም (مبدل منه) በሙሉ ሁኔታው (ِإِعْرَابِه) ይከተለዋል። ማለትም "ተከታይ አስከታዩን ይከተላል" التابع يتبع متبوعه ስለተባለ የመጀመሪው ስሙ (مبدل منه) ረፍዕ ከሆነ በደሉም (ተለዋጩም) ረፍዕ ይሆናል፤ ነስብ ከሆነም ነስብ ይሆናል፤ ኸፍድ ከሆነም ኸፍድ ይሆናል።
✔የ4ቱንም አይነት ተላዋጭ ስም (በደልبَدَل) ምሳሌ እንይ።
①፡ بَدَلُ اَلشَّيْءِ مِنْ اَلشَّيْءِ (አንድ ነገር በአንድ ነገር ሲለወጥ) ወይም (بدل الكل بالكل) ይባላል
ምሳሌ፡ قَامَ زَيْدٌ أَخُوكَ (ዘይድ ወንድምህ ቆመ)
②፡ بَدَلُ الْبَعْضِ مِن الْكُلِّ (ከሙሉ ላይ ከፊሉ ሲለወጥ)
ምሳሌ፡ أَكَلْتُ اَلرَّغِيفَ ثُلُثَهُ (ምግቡን አንድ ሶስተኛውን በላሁት)
☞ ይህ የበደል አይነት ብዙ ጊዜ መጨረሻው ሙብደሉን ከሚጠቁም ዶሚር (የተውላጠ-ስም ቅጥያ) ጋር የተያያዘ ነው።
③፡ بَدَلُ الِاشْتِمَال (በጠቅላለው ሲለወጥ)
ምሳሌ፡ نَفَعَنِي زَيْدٌ عِلْمُهُ (ዘይድ እውቀቱ ጠቀመኝ)
* ይሄኛው የበደል አይነት ሌላ የሙብደል ክፍል ሳይቀድመው በመሀል የሚቀመጥ ሲሆን መጨረሻው ሙብደሉን (مبدل) ከሚጠቁም ዶሚር (የተውላጠ-ስም ቅጥያ) ጋር የተያያዘ ነው።
④፡ بَدَلُ اَلْغَلَطِ (በስህተት የተለወጠ)
ምሳሌ፡ رَأَيْتُ زَيْدًا اَلْفَرَسَ (ዘይድን ፈረስ አየሁ)
፡[أَرَدْتَ أَنْ تَقُولَ رَأَيْتُ اَلْفَرَسَ فَغَلِطْتَ فَأَبْدَلْتَ زَيْدًا مِنْه] [ያሰብከው ወይም የፈለከው ፈረስ አየሁ ለማለት ነበር ነገር ግን በምላስ ስህተት "ዘይድን አየሁ" ትልና ከዚይም መልሰህ በማስተካከል "ፈረስ አየሁ" ትላለህ ማለት ነው]
✔ግስ በግስ ሲለወጥ (بدل فعل من فعل) ምሳሌ»
☞፡ "من يشكر ربَّهُ يسجد له يَفُزْ" (ጌታውን የሚያመሰግን ይሰግዳል ይድናል)
------------------------------- ✔ሙብተዳእ እና ኸበር… (المُبْتَدَأ والخَبَر)
* ሙብተዳእ (مُبْتَدَأ) ማለት በንግግር "የተጀመረ" ማለት ሲሆን ኸበር (خَبَر) ማለት ደግሞ የተጀመረውን የሚጨርስ ወይም የሚያሟላ ማለት ነው። ምሳሌ اللُه ብለን ዝም ካልን አድማጭ ይጠብቃል ስለዚህ "الله" የሚለውን የሚያሟላ ለምሳሌ غَفُور ብንል ኸበር (خبر) ይሆናል። «اللهُ غَفُور» ስንል ሙብተዳውና ኸበሩ ተሟላ ማለት ነው።
♦ሙተዳእ እና ኸበር (المبتدأ والخبر) ከ7ቱ መርፊዓቶች ስለሆኑ ከፊታቸው ህጉን የሚለውጥ ነገር (عَوَامِل) እስካልመጣባቸው ድረስ ህጋቸው መርፉዕ (مرفوع) ነው። [ህጉን የሚለውጥ ነገር ማለት (عَوَامِل) ለምሳሌ إنّ]
* ኢዕራቡ ሲተዓረብ እንዲህ ነው»
[مبتدأ مرفوع بالابتداء]
[والخبر مرفوع بالمبتدأ]
♦ልክ እንደ "ፋዒል" እና "ናኢበል-ፋዒል" ሙብተዳም በ2 ይከፈላል።
① በግልፅ/ظاهر የመጣ
☞ምሳሌ፡ الله غفور ያልነው ላይ "الله" የሚለው ግልፅظاهر ሙብተዳእمبتدأ ነው።
② በተውላጠ-ስም ተተክቶ የመጣ (مضمر)
☞ምሳሌ፡ أنا الله ስንል "أنا" ሙብተዳእمبتدأ ሲሆን "الله" ያለው ኸበር خبر ይሆናል።
* 12ቱ ተውላጠ ስሞች (ضماءر) እነዚህ ናቸው፡-
[أَنَا ، نَحْنُ ، أَنْتَ ، أَنْتِ ،أَنْتُمَا ، أْنُتُمْ ، أَنْتُنَّ ، هُوَ ، هِيَ ، هُمَا ، هُمْ ، هُنَّ]
☞ ቡሗላ (መጨረሻ ላይ) የሚታዩ የሙብተዳእ እና የኸበር ርዕሶች»
♦ኸበርخبر ነጠላ (مُفْرَد) እና ነጠላ ያልሆነ (غَيْرُ مُفْرَد)
♦ የወደቀ(محذوف) ሙብተዳእ እና ኸበር።
♦ ሙብተዳእና ኸበር በጁምላ ወይም በአረፍተነገር (الجملة)
--------------------------- ✔የሙብተዳእ እና የኸበር ህግ ቀያሪዎች… ክፍል-4
፡ (عوامل الداخلة على المبتدأ والخبر)
* የሙብተዳእና የኸበርን ሁኔታ የሚለውጡ ነገሮች 3 ናቸው።
① ካነ (َكَان) እና ወንድሞቿ [كَانَ وَأَخَوَاتُهَا]
② ኢንነ (إنَّ) እና ወንድሞቿ [إِنَّ وَأَخَوَاتُهَا]
③ ዞነንቱ (ظَنَنْتُ) እና ወንድሞቿ [ظَنَنْتُ وَأَخَوَاتُهَا]
* የሙብተዳእና የኸበር ስም ላይ كَان ወይም إنَّ ቀድመው ሲገቡ ነባሩን ህግ (መርፉዕነቱን) ይለውጡታል። ምሳሌ»
♦የካነ ስምاسم كان እና የኢንነ ኸበር خَبَرُ إنَّ መርፉእ ናቸው።
✔የካነ ስም (اسم كان) ህጉ መርፉዕ (مرفوع)ነው።
☞ምሳሌ كَانَ اللهُ غَفُورًا ስንል اللهُ የሚለው የካነ ስምاسم كان ስለሆነ መርፉዕ ሆኗል። [غَفُورًا ኸበሩ ካነ خبر كان መንሱብ]
✔የኢንነ ኸበር (خَبَرُ إنَّ) ህጉ መርፉዕ (مرفوع)ነው።
☞ምሳሌ إنَّ اللهَ غَفُورٌ ስንል غَفُورٌ የሚለው የኢንነ ኸበር خبر إنَّ ስለሆነ መርፉዕ ሆኗል።
♦ማስታወሻ፡ የመንሱባት ክፍል (المنصوبات) ላይ የሚታዩ የكَان እና የإنَّ ህጎች»
✔የካነ ኸበር (َخَبَرُ كَان) ህጉ መንሱብ (منصوب) ነው።
☞ምሳሌ [غَفُورٌ የካነ ኸበር خَبَرُ كَان ስለሆነ መንሱብ ሆኗል]
✔የኢንነ ሰም (إسْمُ إنَّ) ህጉ መንሱብ (منصوب) ነው።
☞ምሳሌ [اللهَ የኢንነ ስም اسم إنَّ ስለሆነ መንሱብ ሆኗል]
♥ ለሌሎቹም የكَان እና የإنَّ ወንድሞች ህጋቸው በዚህ መሰረት መርፉዕ (مرفوع)ነው።።
♦፡የكَان ወንድሞች (أخواة كان)
☞፡ [أَمْسَى، أَصْبَحَ، أَضْحَى، ظَلَّ، بَاتَ، صَارَ، لَيْسَ، مَا زَالَ، مَا اِنْفَكَّ، مَا فَتِئَ، مَا بَرِحَ، مَا دَامَ، مَا تَصَرَّفَ مِنْهَا نَحْوَ كَانَ، وَيَكُونُ، كُنْ، أَصْبَحَ ، يُصْبِحُ ، أَصْبِحْ]
♦፡የإنَّ ወንድሞች (أخواة إنَّ)
☞፡ [إِنَّ، أَنَّ، لَكِنَّ، كَأَنَّ، لَيْتَ، لَعَلَّ]

1 comment:
We thank you in the name of Allah
Post a Comment